ቀጥታ፡

ዓለም አቀፍ የመኪና አምራቾች በኢትዮጵያ በዘርፉ ያሉ እድሎችን ተጠቅመው መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ተጠየቀ

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 24/2015 (ኢዜአ)፦ ዓለም አቀፍ የመኪና አምራቾች በኢትዮጵያ በዘርፉ ያሉ እድሎችን ተጠቅመው መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ገለጹ።

አምባሳደር ተፈራ ከቻይናው የመኪና አምራች ኩባንያ ቼሪ ኮሜርሻል ባለቤት ጂን ሱዊ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ አምባሳደሩ በመኪና ማምረት ዘርፍ በኢትዮጵያ ያሉ አማራጮችን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።


ኩባንያውን ጨምሮ ዓለም አቀፍ የመኪና አምራቾች በኢትዮጵያ ያሉ እድሎችን ተጠቅመው መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ ማቅረባቸውን በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም