በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ከኤር አልጀሪ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ከኤር አልጀሪ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 24/2015 (ኢዜአ) ፦ በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ከአልጄሪያ ብሔራዊ አየር መንገድ ኤር አልጀሪ ዋና ዳይሬክተር ያሲን ቤንስሊማኔ ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ ሁለቱ አገራት በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ መሆኑን አምባሳደር ነቢያት ገልጸዋል።
በተለይም በአዲስ አበባ እና አልጀርስ መካከል ቀጥታ በረራ ለመጀመር ከስምምነት ላይ መደረሱንና በረራው የሁለቱን አገራት የንግድ ትብብር ለማጎልበት እንደሚያስችል አመልክተዋል።
እ.አ.አ በ1962 የተቋቋመው ኤር አልጀሪ ከ70 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች አሉት።