የዲስትሪክቱ አመራሮችና ሠራተኞች ከ20 ሺህ በላይ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ - ኢዜአ አማርኛ
የዲስትሪክቱ አመራሮችና ሠራተኞች ከ20 ሺህ በላይ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ
ጅግጅጋ ፤ ሐምሌ 23/2015 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጅግጅጋ ዲስትሪክት አመራሮችና ሠራተኞች "ነገን ዛሬ እንትከል" በሚል መሪ ሀሳብ የአራንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር አካሄዱ።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጅግጅጋ ዲስትሪክት ስር የሚገኙ ቅርንጫፍ ባንኮች አመራሮችና ስራተኞች በጅግጅጋ ከተማ በባንኮች ቅጥር ግቢ ጨምሮ በጅግጅጋ ከተማ ቀበሌ 12 በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በተገነባ ካህ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና በጅግጅጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከ20 ሺህ በላይ ችግኞችን ዛሬ ተክለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጅግጅጋ ዲስትሪክት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀይሉ ዘር በክልሉ የተጀመረውን 2ኛውን ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ስኬታማ ለማድረግ በዲስትሪክቱ ስር የሚገኙ ባንኮች አመራሮች ሰራተኞች ችግኝ ተከላ አካሂደዋል።
የተተከሉት ችግኞች በዋናነት ለውበትና ለኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው መሆናቸውን አመልክተዋል።
የዲስትሪክቱ ባልደረባ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ በመሳተፍ አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖራቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ወይዘሮ ዘመን ታችበሌ በበኩላቸው ለተከሏቸው ችግኞች አስፈላጊውን እንክብካቤ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በክልሉ 53 ቅርንጫፍ ባንኮችን በማቋቋም የህብረተቡ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ የዲስትሪክቱ ዋና ዳይሬክተር አስታውቀዋል።