ኢትዮጵያ ከአውስትራሊያ ጋር ያላትን ለረጅም ጊዜ የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ትሰራለች- አምባሳደር ሃደራ አበራ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ከአውስትራሊያ ጋር ያላትን ለረጅም ጊዜ የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ትሰራለች- አምባሳደር ሃደራ አበራ
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 21/2015(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ከአውስትራሊያ ጋር ያላትን ለረጅም ጊዜ የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትሰራ በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሃደራ አበራ ገለጹ።
አምባሳደር ሃደራ ለአውስትራሊያ ጋቨርነር ጀነራል ዴቪድ ሁርሌይ የሹመት ደብዳቤ አቅርበዋል።
ሁለቱ ባለስልጣናት የሁለቱን አገራት ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል።
በኢትዮጵያና በአውስትራሊያ መካከል ያለውን የረጅም ዘመን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር አበክረው እንደሚሰሩ አምባሳደር ሃደራ ገልጸዋል።
ጋቨርነር ጀነራል ዴቬድ ሁርሌይ የአምባሳደሩ ተልዕኮ የተሳካ እንዲሆን የአውስትራሊያ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ እና አውስትራሊያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እ.አ.አ በ1954 ነው።