የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በግብጽ አዲስ እየተገነባ ያለውን የካይሮ ከተማ ( New Cairo city) ጎበኘ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በግብጽ አዲስ እየተገነባ ያለውን የካይሮ ከተማ ( New Cairo city) ጎበኘ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 20/2015(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በግብጽ አዲስ እየተገነባ ያለውን የካይሮ ከተማ ( New Cairo city) ጎበኝቷል።
ከተለያዩ ከተሞችና ተቋማት የተውጣጣው የልዑካን ቡድን የካይሮ ከተማን የሕዝብ ብዛት መጨናነቅ ለማስተንፈስ መልሶ የማልማትና ለወደፊቱ ትውልድ የሚሆን ዘመናዊ ፣ ሁለገብ ና ምቹ ከተማን ለመገንባት የተሠሩ ሥራዎችን ጎብኝቷል።
ጥንታዊነትን ከዘመናዊነት፤ ገጠርን ከከተማ አስማምቶ ለማደግ የተከናወኑ ተግባራትንም ተመልክቷል።
በጉብኝቱ ወቅት ከካይሮ ከተማ አስተዳደር ጋር ከተሞችን በማዘመን፣ ወቅቱን የዋጀ የከተማ እና የመሠረተ ልማት ግንባታን፣ እንዲሁም የተጨናነቁ የከተማ አካባቢዎችን ስለማስተካከል በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።
ኢትዮጵያና ግብጽ በባህል፣ በታሪክና በሕዝብ ብዛት ተቀራራቢነት ያላቸው በመሆኑ የልዑካን ቡድኑ ያገኘው ልምድ በየከተሞቹ ሊተገበሩ የሚችሉ መሆናቸውን አባላቱ ገልጸዋል።
ጉብኝቱ ሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓ.ም የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በግብጽ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ የተከናወነ መሆኑም ተገልጿል።
በጉብኝቱ የፌዴራል አመራሮች ፣ የአዲስ አበባ፣ የአዳማ፣ የባሕር ዳርና የሐዋሳ ከተሞች ከንቲባዎችም ተሳትፈዋል።