በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረ መስቀል ጫላ የተመራ ልዑክ በጄኔቫ የስራ ጉብኝት እያደረገ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረ መስቀል ጫላ የተመራ ልዑክ በጄኔቫ የስራ ጉብኝት እያደረገ ነው
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 19/2015 (ኢዜአ)፡- በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረ መስቀል ጫላ የተመራ ልዑክ ኢትዮጵያ ለዓለም ንግድ ድርጅት(WTO) አባልነት እያካሄደች ላለችው እንቅስቃሴ አጋዥ ነው የተባለ ጉብኝት በስዊዘርላንድ ጄኔቫ በማድረግ ላይ ይገኛል።
በውይይቱ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጄኔቫ ቢሮ እና በስዊዘርላንድ የሚገኙ ዓለም አቀፍ ተቋማት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ፀጋአብ ክበበው ተገኝተዋል።
ልዑካን ቡድኑ ጄኔቫ የሚገኝውን የዓለም የንግድ ድርጅት ጽህፈት ቤትን ጎብኝቷል።
ቡድኑ የዓለም ንግድ ድርጅት ጽህፈት ቤት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ ከተመረጡ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል አገራት እና ድርጅቱን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ከሚገኙ አገሮችና የልማት አጋሮች ጋር ምክክር አድርጓል።
ልዑካን ቡድኑ በጄኔቫ ለሶስት ቀናት የሚቆይ መሆኑ ተገልጿል።