በሴካፋ ከ18 ዓመት በታች የሴቶች እግር ኳስ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሽንፈት ገጥሞታል - ኢዜአ አማርኛ
በሴካፋ ከ18 ዓመት በታች የሴቶች እግር ኳስ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሽንፈት ገጥሞታል
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 18/2015(ኢዜአ)፡- በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ ማህበራት ምክር ቤት(ሴካፋ) ከ18 ዓመት በታች እግር ኳስ ውድድር ማምሻውን ጨዋታውን ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዩጋንዳ አቻው 1 ለ 0 ተሸንፏል።
ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው ከ18 ዓመት በታች ውድድር ዛሬ በታንዛንያ ዳሬ ሰላም ተጀምሯል።
10 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው ቻማዚ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዩጋንዳ አለንስ ናሳዚ በ68ኛው ደቂቃ ባስቆጠረችው ግብ ኢትዮጵያን 1 ለ 0 አሸንፋለች።
በአሰልጣኝ እንዳልካቸው ጫካ የሚመራው ብሔራዊ ቡድን ቀጣይ ጨዋታውን ከነገ በስቲያ ከውድድሩ አስተናጋጅ ታንዛኒያ ጋር ያደርጋል።
ቀን በተካሄደው የውድድሩ መክፈቻ ጨዋታ አስተናጋጇ አገር ታንዛንያ ብሩንዲን 3 ለ 0 አሸንፋለች።