የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ፤ ከጀርመን የልማት ሚኒስትር ጆከን ፍላዝባርት ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ፤ ከጀርመን የልማት ሚኒስትር ጆከን ፍላዝባርት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 18/2015 (ኢዜአ)፡- የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ፤ ከጀርመን የልማት ሚኒስትር ጆከን ፍላዝባርት ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ።
የሁለቱ አገራት ሚኒስትሮች የሁለትዮሽ ውይይቱን ያደረጉት በጣሊያን ሮም እየተካሄደ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሥርአተ-ምግብ ሽግግር ጉባኤ ጎን ለጎን ነው።
በውይይቱ ኢትዮጵያ በግብርና ልማት ላይ እያከናወነቻቸው ያሉ ውጤታማ ስራዎች እና በዘርፉ በጋራ መስራት የሚያስችሉ ጉዳዮች ተነስተዋል።
ጀርመን የኢትዮጵያን የግብርና ስራዎች በማዘመን በኩል የተለያዩ ድጋፍና እገዛዎችን እያደረገች መሆኑ ይታወቃል።
የኢትዮጵያ እና የጀርመን የሁለትዮሽ የዲፕሎማሲ ግንኙነት የተጀመረው እ.ኤ.አ 1905 መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።