ቀጥታ፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራው ከፍተኛ ልዑክ ዳሬሰላም በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አረንጓዴ አሻራውን አኖረ

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 17/2015 (ኢዜአ):- በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራው ልዑክ ዳሬሰላም በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

ልዑኩ ታንዛንያ በሚካሄደው የአፍሪካ የሰው ኃይል ልማት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ከቀትር በኋላ ዳሬሰላም መግባቱ ይታወቃል።

በጉባኤው ላይ የሚሳተፈው ልዑክ በዳሬሰላም የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የጎበኘ ሲሆን በኤምባሲው ቅጥር ግቢ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር አካል የሆነ የችግኝ ተከላ አካሄዷል።

የአፍሪካ የሰው ኃይል ልማት የመሪዎች ጉባኤ ነገ እና ከነገ በስቲያ ይደረጋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም