በዩናይትድ ኪንግደም የሚኖሩ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት የኢትዮጵያን ፍላጎቶች ማስጠበቅ ላይ በትኩረት እንደሚሰሩ ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
በዩናይትድ ኪንግደም የሚኖሩ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት የኢትዮጵያን ፍላጎቶች ማስጠበቅ ላይ በትኩረት እንደሚሰሩ ገለጹ
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 17/2015 (ኢዜአ):- በዩናይትድ ኪንግደም የሚኖሩ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት የኢትዮጵያን ፍላጎቶች ማስጠበቅ ላይ በትኩረት እንደሚሰሩ አስታወቁ።
በዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደር ተፈሪ መለሰ በአገሪቷ ከሚገኙ የዳያስፖራ ማህበረስብ አባላት ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።
በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ገለጻ አድርገዋል።
በዩናይትድ ኪንግደም የሚኖሩ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት የኢትዮጵያን ፍላጎቶች በሚያስጠብቁ ስራዎች ላይ ከኤምባሲው ጋር በትብብር እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።