የኢትዮ-ተርኪዬ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በኢስታንቡል ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮ-ተርኪዬ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በኢስታንቡል ይካሄዳል
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 17/2015 (ኢዜአ):- የኢትዮ-ተርኪዬ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በተያዘው የፈረንጆች ዓመት በኢስታንቡል ከተማ እንደሚካሄድ ተገለጸ።
በተርኪዬ የኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሐመድ ከኢስታንቡል የንግድ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አህመት ኦዜር እና ከኢንስታንቡል ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ሃካን አኪን ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ በኢስታንቡል የሚካሄደው የኢትዮ-ተርኪዬ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ያተኮረ መሆኑ ተጠቁሟል።
ምክር ቤቶቹ ፎረሙን አንካራ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በትብብር ለማዘጋጀት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።