በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ የቻይና ባለሀብቶች የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የስራ እንቅስቃሴን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ የቻይና ባለሀብቶች የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የስራ እንቅስቃሴን ጎበኙ
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 17/2015 (ኢዜአ) :- በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ 20 የቻይና ባለሀብቶች የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የስራ እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል።
ባለሀብቶቹ የምርት ገበያውን አሰራር አስመልክቶ ከተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድማገኘሁ ነገራ ጋር ተወያይተዋል።
አቶ ወንድማገኘሁ በምርት ገበያው ከሚገበያዩ ምርቶች አብዛኞቹ ወደ ቻይና የሚላኩ በመሆናቸው እሴት በሚጨምር መስክ ቢሰማሩ አዋጭ እንደሆነ ገልጸውላቸዋል።
ባለሀብቶቹም ጠቃሚ መረጃ እንዳገኙና ከምርት ገበያው ጋር ተቀራርበው ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው አመልክተዋል።