በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ ልዑክ ታንዛንያ ገባ - ኢዜአ አማርኛ
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ ልዑክ ታንዛንያ ገባ
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 17/2015 (ኢዜአ) :- በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ ልዑክ ታንዛንያ በሚካሄደው የአፍሪካ የሰው ኃይል ልማት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዳሬሰላም ገብቷል።
ልዑኩ ጁሊየስ ኔሬሬ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የታንዛንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምባሩክ ምባሩክ፣ በታንዛንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሽብሩ ማሞ እና ዲፕሎማቶች አቀባበል አድርገውለታል።
የአፍሪካ የሰው ኃይል ልማት የመሪዎች ጉባኤ ነገ እና ከነገ በስቲያ በዳሬ ሰላም ይካሄዳል።