ቀጥታ፡

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ ተመለከቱ

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 17/2015(ኢዜአ):- የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ ተመልክተዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ከትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ጋር በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢና በ4 ኪሎ ሳይንስ ፋካሊቲ ተገኝተው ተፈታኝ ተማሪዎችን አበረታተዋል።

በዩኒቨርሲቲዎቹ ያለውን የተማሪ አቀባበል፣ የመኝታና የመመገቢያ ቦታዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።


 

በምልከታቸውም ተፈታኝ ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲሰሩ ሚኒስትሩ አበረታተዋል።

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 19/2015 ጀምሮ ይሰጣል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም