ቀጥታ፡

የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ በመግባት ላይ ናቸው

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 16/2015 (ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ በመግባት ላይ ይገኛሉ።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሁለት ዙር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ በትምህርት ሚኒስቴር መገለጹ ይታወቃል።


 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲና ፌደራል ቴክኒክና ስልጠና ኢንስቲትዩት ይሰጣል።

ከ11ዱም ክፍለ ከተማ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡

ከመፈተኛ ጣቢያዎች አንዱ በሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመግባት ላይ የሚገኙ ሲሆን በቦታው ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመገኘት ተማሪዎችን አበረታተዋል፡፡


 

የዘንድሮ ዓመት የ12ኛ ክፍል ፈተና በአዲስ አበባ ደረጃ በ11 የመፈተኛ ጣቢያዎች 24 ሺህ 775 የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 19 እስከ 21 እንዲሁም 28 ሺህ 751 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 25 እስከ 28/ 2015 ዓ. ም ድረስ ፈተናውን እንደሚወሰዱ የከተማው ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም