የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ በተለያየ የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ በተለያየ የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 15/2015(ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ በተለያየ የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።
የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ፍቅሬ ደሳለኝ እንደገለጹት ዩኒቨርስቲው ያስመረቃቸው 2377 ተማሪዎች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ በተለያየ የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸው ናቸው።
ከተመራቂ ተማሪዎች መካከልም የጎረቤት ደቡብ ሱዳንን ተማሪዎች ይገኙበታል።
በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሣሙኤል ክፍሌ ለተመራቂዎቹ የዶክትሬት ተመራቂዎችን የማልበስ ስነ ስርአት ያካሄዱ ሲሆን በውጤታቸው ከፍተኛ ነጥብ ላስመዘገቡትም ዲግሪ ሰጥተዋል።