የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ - ኢዜአ አማርኛ
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ
አዳማ፤ ሐምሌ 15/2015(ኢዜአ):- የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ።
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በአገሪቱ ውስጥ ትምህርት ቤቶችን በማስፋፋት በተለይም ከበጎ አድራጊ ድርጅቶች ባገኙት ገንዘብ 27 ሁለተኛና አዳሪ ትምህርት ቤቶችን አስገንብተዋል።
ትምህርት ቤቶቹ በርካታ ተማሪዎች መቀበል እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን ትምህርት ቤቶቹም ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸው ተመልክቷል።
ትምህርት ቤቶቹ በኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በአማራ፣ በአዲስ አበባ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በጋምቤላ ክልሎች መገንባታቸውም ታውቋል።
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በትምህርትና በሰብዓዊ ልማት ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ዶክትሬቱ እንደተሰጣቸውም በወቅቱ ተገልጿል።