ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ ከቻይና ጄዲ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ልዑክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 15/2015(ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ ከቻይና ጄዲ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይታቸውም በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት እድሎችና አማራጮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተመላክቷል።

በዚህም ኩባንያው በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በተለይም በኢ-ኮሜርስ፣ በዲጂታል የፋይናንስ ስርዓት እና በአይ ሲ ቲ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ለመሰማራት እቅድ እንዳለው ገልጿል።

በተጨማሪም ኩባንያው የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት እድሎችና አማራጮች የመቃኘት እቅድ እንዳለው መግለጹን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም