ኢጋድ እና ኦቻ በምስራቅ አፍሪካ የሰብአዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢጋድ እና ኦቻ በምስራቅ አፍሪካ የሰብአዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 14/2015(ኢዜአ):- የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት(ኦቻ) በምስራቅ አፍሪካ የሰብአዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
ውይይቱን ያደረጉት የኢጋድ የሰላም እና ደህንነት ዘርፍ ዳይሬክተር ሲራጅ ፈጌሳ እና የኦቻ የኢትዮጵያ ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ ሚሼል ሳድ ናቸው።
አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ለኦቻ የኢትዮጵያ ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ ሚሼል ሳድ በሱዳን እና በቀጣናው ስላለው የሰብአዊ ሁኔታ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ሁለቱ ተቋማት በቀጣናው ያሉትን የሰብአዊ ሁኔታዎች ምላሽ መስጠት በሚያስችላቸው አማራጮች ላይ በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።