የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክተር ዋንግ ዪ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክተር ዋንግ ዪ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 14/2015(ኢዜአ):- የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክተር ዋንግ ዪ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ዋንግ ዩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በቆይታቸውም ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር የኢትዮጵያና የቻይና ሁለንተናዊ ስትራቴጂካዊ የትብብር አጋርነት የበለጠ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ ይመክራሉም ተብሏል።
ኃላፊው ቀደም ሲል የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።