እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለድምጻዊት እጅጋየሁ ሽባባው የክብር ዶክትሬት ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 13/2015(ኢዜአ):- እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለድምጻዊት እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።

ዩኒቨርሲቲው በአራተኛ ዙር በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ መርሐ-ግብር ያሰለጠናቸውን 750 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።

በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል፡፡

ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን የተከታተሉት በዩኒቨርሲቲው በሚገኙ ስድስት ኮሌጆች ውስጥ ነው።
 

ከተመራቂዎቹ መካከል በአማራ ፖሊስ ኮሌጅ በመምህርነት በከፍተኛ ዲፕሎማ ፕሮግራም ስልጠና የወሰዱ መምህራን ይገኙበታል።

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ለድምጻዊት እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ) የክብር ዶክትሬት አበርክቶላታል።

ዩኒቨርሲቲው ለጂጂ የክብር ዶክትሬቱን የሰጠው የኢትዮጵያን ባህልና ሙዚቃ ለዓለም በማስተዋወቅ እንዲሁም በኪነ ጥበብ የአዊን ሕዝብ ቋንቋ እና ባህል በማሳደግ ላበረከተችው አስተዋፅኦ መሆኑን ገልጿል።

የክብር ዶክትሬቱን የእጅጋየሁ ሽባባው ቤተሰቦች ተቀብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም