ቀጥታ፡

የጤና አውደ-ርዕዩ  ኢትዮጵያን በዘርፉ እያስመዘገበች ያለውን ስኬት ያሳየና የቀጣይ ዕቅዶችንም ያመላከተ ነው -የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ

አዲስ አበባ ሐምሌ 11/2015(ኢዜአ ) የጤና አውደ-ርዕዩ  ኢትዮጵያን በዘርፉ እያስመዘገበች ያለውን ስኬት ያሳየና የቀጣይ ዕቅዶችንም ያመላከተ መሆኑን የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ገለጹ፡፡

የሐረሪ ክልል የጤና ቢሮ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የጤና አውደ-ርዕይ ዛሬ ጎብኝተዋል።

ከጉብኝቱ በኃላ ኢዜአ ያነጋገራቸው የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ኤሊያስ ዩኑስ፤ አውደ-ርዕዩ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ከራሷ አልፋ ለዓለም የጤና ቱሪዝም መዳረሻ ለመሆን እየሰራች መሆኑን ያመላከተ ነው ብለዋል።

በዘርፉ እያስመዘገበች ያለውን ስኬት ያሳየና የቀጣይ ዕቅዶችንም ያመላከተ መሆኑን ጠቅሰው፤ የክልሉ ጤና ቢሮ ብዙ ልምድና ተሞክሮዎችን ማግኘቱንም ተናግረዋል።

ከጉብኝቱ ተሳታፊዎች መካከል ያነጋገርናቸው የጤና ባለሙያዎች አውደ-ርዕዩ የኢትዮጵያ የሕክምና ዘርፍ ዕድሎች፣ የቴክኖሎጂ እድገቱንና የቀጣይ ተስፋዎችን ጭምር ያመላከተ መሆኑን ገልፀዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም