ቀጥታ፡

በአንድ ጀምበር የ500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ-ግብር በአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ተከናወነ

 

አዲስ አበባ ሐምሌ 10/2015(ኢዜአ):-በአንድ ጀምበር የ500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ-ግብር በአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ተከናውኗል።

በአየር ኃይል ደረጃ በተከናወነው ችግኝ የመትከል መርሐ-ግብር የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ከቢሾፍቱ ከተማ የተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎችና የአየር ኃይል አባላት ተገኝተዋል።


 

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለነገው ትውልድ የምትሆን የለማች ጠንካራ አገር ለመገንባት ለተያዘው ራዕይና ግብ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።


 

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በበኩላቸው ዓለም በአየር ንብረት መዛባት በጦርነት በወረርሽኝና በሌሎች ችግሮች መወጠሯንና ይህም ከበረሃማነት ጋር ተያይዞ የሚከሰት ችግር መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡


 

ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅ ለተያዘው አገራዊ የአረንጓዴ ልማት ንቅናቄ ችግኝ መትከል አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ፍቃዱ ሰራዊቱ ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክበው ለታለመለት ዓላማ ከግብ በማድረሱ ረገድም እንደ ከዚህ ቀደሙ ጥረታቸውን መቀጠል እንዳለባቸው መግለጻቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም