የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ለአገር እድገት መሰረት በመጣል የቀጣዩን ትውልድ የምጣኔ ሃብት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው-የኢኮኖሚ ባለሙያ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ለአገር እድገት መሰረት በመጣል የቀጣዩን ትውልድ የምጣኔ ሃብት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው-የኢኮኖሚ ባለሙያ
አዲስ አበባ ሐምሌ 9/2015(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ለአገር እድገት መሰረት በመጣል የቀጣዩን ትውልድ የምጣኔ ሃብት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ኢዜአ ያነጋገራቸው አንድ የኢኮኖሚ ባለሙያ ተናገሩ።
ኢትዮጵያ ባለፉት አራት ዓመታት ከ25 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል በስኬት ቀጥላ ሁለተኛውን ምዕራፍ ዘንድሮ ጀምራለች።
የሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አካል የሆነው የአንድ ጀምበር የ500 ሚሊዮን የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብርም በነገው እለት በአገር አቀፍ ደረጃ ይከናወናል።
ከዚሁ ጋር በተገናኘ ኢዜአ ያነጋገራቸው የኢኮኖሚ ባለሙያው ደረጄ ደጀኔ፤ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ለአገር እድገት መሰረት በመጣል የቀጣዩን ትውልድ የምጣኔ ሃብት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ተናግረዋል።
በመሆኑም ለዚህ አገራዊ ዓላማ ስኬት ዜጎች ሁሉ የድርሻቸውን አስተዋጽኦ በማድረግ ዘመን የሚሻገር አሻራቸውን ማሳረፍ አለባቸው ብለዋል።
በአረንጓዴ አሻራ ልማት የተያዘውን አቅድ ለማሳካት ችግኞችን ከመትከል ባለፈ በመንከባከቡ ተግባር ላይ ሁላችንም አስተዋጽኦ ልናደረግ ይገባናል ነው ያሉት።
በቀጣናው ያለውን የልማትና የኢኮኖሚ ትስስር በማጠናከር በኩል የአረንጓዴ ልማት የላቀ ሚና አንዳለው የጠቀሱት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው የኢትዮጵያን ተሞክሮ የአካባቢው አገራትም ሊጋሩት ይገባል ብለዋል።
የሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በይፋ ከተጀመረ ጀምሮ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ ቀጥሏል።
የዚሁ መርሃ-ግብር አካል የሆነው የአንድ ጀምበር የ500 ሚሊዮን የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብርም በነገው እለት በአገር አቀፍ ደረጃ ይከናወናል።