ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራሮችና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ ሀምሌ 7/2015(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራሮችና ሠራተኞች በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ። 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ተቋሙ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ባለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ተሳትፎውን ቀጥሏል።


 

ይህንንም ተከትሎ በዘንድሮ የክረምት ወቅት ተቋሙ 100 ሺህ ችግኞችን በተለያዩ ሥፍራዎች ለመትከል አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቆ ወደ ሥራ ገብቷል ብለዋል።  

በዚህም የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች በዛሬው ዕለት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በመገኘት አረንጓዴ አሻራቸውን ማኖራቸውን ተናግረዋል። 

የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡና በቀጣይም የአረንጓዴ አሻራ ተሳትፎውን አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።   

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም