የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሐ-ግብሮች ያሰለጠናቸውን የፖሊስ መኮንኖች አስመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሐ-ግብሮች ያሰለጠናቸውን የፖሊስ መኮንኖች አስመረቀ
አዲስ አበባ ሐምሌ 8/2015 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ መርሐ-ግብሮች ያሰለጠናቸውን የፖሊስ መኮንኖች ዛሬ በሰንዳፋ ማስመረቁ ተገለጸ።
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤልን ጨምሮ ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች ተገኝተዋል።
ሰልጣኞቹ በፖሊሰ ሳይንስ፣ በስነ-ወንጀልና ወንጀል ፍትሕ እንዲሁም በፖሊስ መኮንንነት ዘርፍ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን ከሰርተፊኬት እስከ ሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸው ተገልጿል።
ከተመራቂዎቹ መካከል በሰላምና ደህንነት እንዲሁም በአስተዳደር ስራ አመራር የተመረቁት ሰልጣኞች ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።