አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ለህንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በብረታ ብረት ኢንዱስትሪና በጋዝ ኢንቨስትመንት ላይ ያሉ እድሎችን የተመለከተ ገለጻ አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ለህንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በብረታ ብረት ኢንዱስትሪና በጋዝ ኢንቨስትመንት ላይ ያሉ እድሎችን የተመለከተ ገለጻ አደረጉ
አዲስ አበባ ሐምሌ 7/2015(ኢዜአ):- በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ለህንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በብረታ ብረት ኢንዱስትሪና በጋዝ ኢንቨስትመንት ላይ ያሉ እድሎችን የተመለከተ ገለጻ እና ውይይት አድርገዋል።
አምባሳደር ደመቀ ገለጻ ያደረጉት ለህንድ የሩዝ ላኪዎች ማህበርና ለህንዱ አክሪቲ ኢንዱስትሪ ኩባንያ መሆኑም ተመላክቷል።
አምባሳደር ደመቀ በኢንቨስትመንት ዘርፎቹ ስላሉ አስቻይ ሁኔታዎች ላይ ከህንዱ የሩዝ ላኪዎች ማህበር ዋና ዳይሬክተር ጉልሻን ራኢ እና ከአክሪቲ ኢንዱስትሪ ኩባንያ ዳይሬክተር ባህራት ቹ ጋር ተወያይተዋል።
በተጨማሪም በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ በማኑፋክቸሪንግ፣ ግብርና እንዲሁም አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችና አበረታች ፓኬጆች ዙሪያ ለባለሀብቶቹ ማብራሪያ መስጠታቸውን በህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።