ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ኬንያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ - ኢዜአ አማርኛ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ኬንያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ
አዲስ አበባ ሐምሌ 5/2015(ኢዜአ):- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ኬንያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
አቶ ደመቀ ነገ እና ከነገ በስቲያ በሚካሄደው 43ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ኬንያ ናይሮቢ መግባታቸው ይታወቃል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከዲፕሎማቶች እና ሰራተኞች ጋር በመሆን በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ችግኝ ተክለዋል።

ችግኝ ተከላው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር አካል መሆኑም ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሁለተኛውን ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር "ነገን ዛሬ እንትከል" በሚል መሪ ሃሳብ በአፋር ክልል ማስጀመራቸው ይታወቃል።
በመርሐ-ግብሩም 25 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዷል።