ቀጥታ፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ኬንያ ገቡ

አዲስ አበባ ሐምሌ 5/2015(ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በ43ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ኬንያ ገብተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጀሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ባጫ ደበሌን ጨምሮ ሌሎች የኬንያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

“የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ሀሳብ ከሐምሌ 6 እስከ 8/2015 በሚካሄደው የምክር ቤቱ ስብስባ የሕብረቱ አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የሕብረቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ ቀጣናዊ የአፍሪካ ተቋማት ኃላፊዎች እና እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም