ቀጥታ፡

እየተሻሻለ የመጣውን የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የሁለትዮሽና የባለ ብዙ ወገን ትብብር በተፋጠነና በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ መሆን ይኖርበታል-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ ሐምሌ 5/2015(ኢዜአ)፦ እየተሻሻለ የመጣውን የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የሁለትዮሽና የባለ ብዙ ወገን ትብብር በተፋጠነና በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ መሆን እንደሚገባው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

አቶ ደመቀ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ውይይታቸው በሁለትዮሽና በወቅታዊው የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ኢጋድ በአዲስ አበባ ያደረገውን ውይይት ኢትዮጵያ በማስተናገዷ አመስግነው የሱዳን ኃይሎች የተኩስ አቁም በማድረግ ለችግሩ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲፈልጉ እና ሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን  እየተሻሻለ የመጣውን የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የሁለትዮሽና የባለ ብዙ ወገን ትብብር በተፋጠነና በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

የሱዳን ሰላም ራሳቸው ሱዳናውያን ባለቤት በሆኑበት በአፍሪካ ሕብረት እና ኢጋድ ማዕቀፍ እንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይ ጥረቶች የተደገፈ ሊሆን እንደሚገባውም አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም