ዳያስፖራው በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋዩን ማፍሰስን ጨምሮ በሌሎች አገራዊ ጉዳዮች ላይ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ይኖርበታል-አምባሳደር ዳባ ደበሌ - ኢዜአ አማርኛ
ዳያስፖራው በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋዩን ማፍሰስን ጨምሮ በሌሎች አገራዊ ጉዳዮች ላይ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ይኖርበታል-አምባሳደር ዳባ ደበሌ
አዲስ አበባ ሐምሌ 4/2015(ኢዜአ)፦ ዳያስፖራው በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋዩን ማፍሰስን ጨምሮ በሌሎች አገራዊ ጉዳዮች ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌ ጠየቁ።
አምባሳደር ዳባ በጃፓን ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በወቅታዊ አገራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ በበይነ-መረብ ውይይት አካሄደዋል።
ዳያስፖራውም ሙያውንና አቅሙን ተጠቅሞ ኢትዮጵያን መደገፍ እንደሚገባው አምባሳደሩ ገልጸዋል።
በአገሩ መዋዕለ-ንዋዩን በማፍሰስ፣ አገራዊ የልማት ስራዎችን በመደገፍ እና የገጽታ ግንባታ ስራዎችን ማከናወንን ጨምሮ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ጉዳይ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።
የዳያስፖራ አባላቱም መንግስት በሁሉም ዘርፍ እያካሄደ ያለውን ሪፎርም እንደሚደግፉ እና ለአገር ያለውን አስተዋጽኦ እንደሚገነዘቡ ተናግረዋል።