ቀጥታ፡

ቤተክርስትያኗ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር  ለተፈናቀሉ ወገኖች 20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገች

መቀሌ ሰኔ 03/2015 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በትግራይ ክልል በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የ20 ሚልዮን ብር ድጋፍ አደረገች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስታን ፓትሪያሪክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ድጋፉን ዛሬ ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ አስረክበዋል።

ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በርክክብ ስነ ስርአቱ ላይ እንዳሉት ድጋፉ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ነው።

“የሃይማኖት መሪዎች ግጭት ሳይሆን ሰላም፣ ውድመት ሳይሆን ልማት ለማረጋገጥ ሃላፊነት አለብን” ያሉት ብፁእነታቸው ወደፊትም አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርእሰ መስተዳድር አቶ  ጌታቸው ረዳ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

የሃይማኖት መሪዎች  ለሰላምና ልማት መረጋገጥ ሚናቸው የላቀ መሆኑን ተናግረዋል።

የተጀመረው መልካም ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም