የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ ከተለያዩ አለም ሀገሮች ከተውጣጡ የሀረሪ ዳያስፖራዎች ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ ከተለያዩ አለም ሀገሮች ከተውጣጡ የሀረሪ ዳያስፖራዎች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ሐምሌ 2/2015(ኢዜአ)፦የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ ከተለያዩ አለም ሀገሮች ከተውጣጡ የሀረሪ ዳያስፖራዎች ጋር በካናዳ ቶሮንቶ ተወያይተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት ውይይቱ በርካታ ብዥታዎችን ያጠራንበት እና በዋና ዋና ሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት የተፈጠረበት ነው ብለዋል።
በተለይም ችግሮችን ከዲያስፖራው ጋር በቅንጅት ከመፍታት ባለፈ በቀጣይም በክልላዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ርብርብ ይደረጋል ብለዋል።

ለ25ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው አለም አቀፍ የሀረሪ ባህልና ስፖርት ፌስቲቫል ስኬታማነት ድጋፍ ላደረጉላቸው አካላት ልባዊ ምስጋና ያቀረቡት ርዕሰ መስተዳደሩ የበአሉ አስተባባሪ የሆኑት የካናዳ ሀረሪ ኮሙኒቲና የሀረሪ ሄሪቴጅ ሴንተር ላደረጉላቸው ደማቅ አቀባበልና መስተንግዶ የላቀ ምስጋና አቀርበዋል።
በውይይቱ ላይም ርዕሰ መስተዳደሩን ጨምሮ የብልጽግና ፓርቲ ሃረሪ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ ፣ የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ አሪፍ መሀመድ ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ግንባታ ማእከል ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ካሊድ አልዋ፣ በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ፣የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሐመድ እንድሪስ፣ በካናዳ እና በአካባቢው የሚኖሩ የሀረሪ ኮሚዩኒቲ ተወካዮች ተገኝተዋል።