የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከእንግሊዙ የአውሮፕላን ሞተር አምራች “ሮልስ ሮይስ” ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከእንግሊዙ የአውሮፕላን ሞተር አምራች “ሮልስ ሮይስ” ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ
አዲስ አበባ ሐምሌ 2/2015 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከእንግሊዙ የአውሮፕላን ሞተር አምራች “ሮልስ ሮይስ” ኩባንያ ጋር ስምምነት መፈራረሙ ተገለፀ።
ስምምነቱ አየር መንገዱ በቀጣይ ለሚረከባቸው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ሞዴል ሞተሮች አጠቃላይ የሰርቪስ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ መረጃ ያመላክታል።