ቀጥታ፡

የሀረሪ ክልል የወረዳ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች የህዳሴ ግድብን ጎበኙ

አዲሰ አበባ ሐምሌ 1/2015(ኢዜአ)፦የሀረሪ ክልል የወረዳ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የግንባታ ሂደትና አሁናዊ ገጽታ ጎብኝተዋል።

አፈ-ጉባኤዎቹ የኢትዮጵያዊያን አሻራ ያረፈበትን ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጎብኘት እድል በማግኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

በጉብኝቱ ላይ የሀረሪ ክልል ምከር ቤት የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ዋቁማ እንዳሉት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያዊያን ትብብርና አንድነት በመገንባት ላይ ያለ የጋራ ፕሮጀክት ነው።

የግድቡን ገጽታና ስራ በቦታው ተገኝተው በመጎብኘታቸው መደሰታቸውንም ገልጸዋል።

ለሀገር ብልጽግና፣ አንድነትና ልማት መሰረት የሆነው የህዳሴ ግድብ ግንባታ በስኬት እንዲጠናቀቅ የሁሉም ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

 

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም