ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በእንግሊዝ የሚገኘውን የኤርባስ A350 አውሮፕላን ክንፍ ማምረቻ ፋብሪካን ጎበኙ

አዲስ አበባ ሐምሌ 1/2015(ኢዜአ):- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና የተቋሙ አመራሮች በእንግሊዝ የሚገኘውን የኤርባስ A350 አውሮፕላን ክንፍ ማምረቻ ፋብሪካን ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱ የተደረገው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እንግሊዝ በረራ ማድረግ የጀመረበትን 50ኛ ዓመት በማስመልከት መሆኑም ተገልጿል።

በእንግሊዝ የኤርባስ A350 አውሮፕላን ክንፍ ማምረቻ ፋብሪካ ስራ ከጀመረ 80 ዓመታት አልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም