የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ለገበታ ለትውልድ ድጋፍ ያደረጉ አካላትን አመሰገነ - ኢዜአ አማርኛ
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ለገበታ ለትውልድ ድጋፍ ያደረጉ አካላትን አመሰገነ
አዲስ አበባ ሐምሌ 1/2015(ኢዜአ):- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ለገበታ ለትውልድ ድጋፍ ያደረጉ አካላትን አመሰገነ።
ጽህፈት ቤቱ በ16ኛ ዙር የምስጋና መልዕክቱ “የገበታ ለትውልድን ጥሪ ተቀብላችሁ ሀላፊነት ስለወሰዳችሁ ለመጪው ትውልድ የምትመጥን ኢትዮጵያን ለመገንባት የድርሻችሁን ስላዋጣችሁ እናመሰግናለን” ብሏል።
ድጋፍ ያደረጉ አካላትም የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ቃል ከገባው 33 ሚሊየን 6 መቶ 60 ሺህ ብር ውስጥ 30 ሚሊየን ገቢ ማድረጉን፣ የፔትሮሊየም አቅራቢ(ፔትሮሊየም ሰፕላይ) ቃል ከገባው 26 ሚሊየን 8 መቶ ሺህ ብር ውስጥ 26 ሚሊየን 8 መቶ 22 ሺህ 6 መቶ 68 ብር ገቢ ማድረጉን፣ መኪያ ኢንተርፕራይዝ ቃል የገባውን 10 ሚሊየን ብር ገቢ ማድረጉን፣ ጌቱ ገለቴ ቃል ከገባው 10 ሚሊየን ብር ውስጥ 5 ሚሊየን ብር ገቢ ማድረጉን፣ ኬሚካል ኢንዱስትሪያል ኮርፖሬሽን ቃል የገባውን 6 ሚሊየን 4 መቶ 32 ሺህ 335 ብር ገቢ ማድረጉን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።