ምክር ቤቱ በሁለተኛ አመት የስራ ዘመኑ ለህዝብ ጠቃሚ አዋጆችን በማፅደቅና አስፈፃሚውን በመቆጣጠር ስኬታማ ስራዎችን አከናውኗል- የአፈጉባኤው አማካሪ - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ በሁለተኛ አመት የስራ ዘመኑ ለህዝብ ጠቃሚ አዋጆችን በማፅደቅና አስፈፃሚውን በመቆጣጠር ስኬታማ ስራዎችን አከናውኗል- የአፈጉባኤው አማካሪ
አዲስ አበባ ሰኔ 30/2015(ኢዜአ)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሁለተኛ አመት የስራ ዘመኑ ለህዝብ ጠቃሚ አዋጆችን በማፅደቅና አስፈፃሚውን በመቆጣጠር ስኬታማ ስራዎችን ማከናወኑን የአፈ-ጉባኤው አማካሪ ዶክተር አብርሃም በርታ ተናገሩ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስፈፃሚውን በመከታተልና በመቆጣጠር ሂደት በዓመቱ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን ማከናወኑን አስታውቋል።
ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት በምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ተወካይና የአፈ-ጉባኤው አማካሪ ዶክተር አብርሃም በርታ፤ 6ኛው ምክር ቤት በ2ኛ አመት የስራ ዘመኑ በህግና ደንብ የተሰጠውን ተግባር በአግባቡ ተወጥቷል ብለዋል።
የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች የተቋማትን የስራ አፈፃፀም በመገምገም፣ በመቆጣጠርና የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወሰዱ በማድረግ ጭምር የተሳካ ስራ ሰርተዋል ነው ያሉት።
በሁለተኛ አመት የስራ ዘመኑ ምክር ቤቱ ለህዝብ ጠቃሚ የሆኑ በርካታ ህጎችን በማውጣትና በማሻሻል፣ አዋጆችን በማጽደቅና አስፈፃሚውን በመቆጣጠር የተሳካ ጊዜ እንደነበረው ገልጸዋል።
በምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች የአስፈጻሚውን አካል ስራዎች በመከታተል፣ በመቆጣጠርና በመገምገም የነበረው ጥረትም የሚደነቅ ነበር ብለዋል።
የመድብለ ፓርቲ ስርአትን ለማጠናከር የሃሳብ ነጻነትን በማስተናገድና የምክር ቤቱን ውሎዎች በቀጥታ ስርጭት ለህዝብ ተደራሽ ማድረግ ተችሏልም ነው ያሉት።
ለአገርና ህዝብ ጠቃሚ በሆኑ አጀንዳዎች ላይ ውይይትና ክርክር በማድረግ ጠቃሚ የሚባሉ ህጎችን በማውጣትና በማሻሻል፣ አዋጆችን በማፅደቅ ጭምር ዓመቱ የተሳካ ነበር ብለዋል ዶክተር አብርሃም።