ቀጥታ፡

የከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ምርምር ተቋማት እና ኢንዱስትሪ ትስስር ረቂቅ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ

አዲስ አበባ ሰኔ 30/2015(ኢዜአ)፦ የከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ምርምር ተቋማት እና ኢንዱስትሪ ትስስር ረቂቅ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል።

አዋጁ በከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ምርምር ተቋማት እና በኢንዱሰትሪው መካከል ምቹ የሆነ ትስስር በመፍጠር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና አለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

አዋጁ የኢንዱስትሪውን መስረታዊ ችግር በመፍታት በቂ እና ብቁ የሰው ኃይል በማፍራት የትስስር ስራዎችን ለመስራት ያለመ መሆኑን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የትስስር ስራዎቹ ሀገራዊ የልማት አጀንዳን ባገናዘበ መልኩ በቅንጅት፣ በወጥነት፣ በተጠያቂነት እና በብቃት እንዲተገበሩ እና ውጤታማነትን፣ የጋራ ተጠቃሚነትን፣ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነትን የሚጨምር እንደሆነም ተገልጿል።

ረቂቅ አዋጁን ባለድርሻ አካላት በየደረጃው ሲወያዩበት ቆይተው በቂ ግብዓት እና ማሻሻያ ተደርጎበት መጽደቁም በመረጃው ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም