የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የክረምት የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሐምሌ 8/2015 ይከፈታል-ፌዴሬሽኑ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የክረምት የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሐምሌ 8/2015 ይከፈታል-ፌዴሬሽኑ
አዲስ አበባ ሰኔ 30/2015(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ወንዶች እና የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የክረምት የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሐምሌ 8 ቀን 2015 እንደሚከፈት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
የዝውውር መስኮቱ እስከ መስከረም 25 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ መሆኑም ታውቋል።
በፕሪሚየር ሊጉ የተጫዋቾች ዝውውር ህጋዊ የሚሆነው በፌዴሬሽኑ ፅሕፈት ቤት በኩል መፈራረም ሲችሉ ብቻ መሆኑን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
በዝውውር ሂደቱ በክልል የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖችን ጨምሮ በሌላ ወገኖች በኩል የሚደረግ የዝውውር ስምምነት ህጋዊ ባለመሆኑ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ነው ፌዴሬሽኑ የገለጸው።
በመሆኑም ሁሉም ክለቦች ህጋዊ አሰራሩን በመከተል ብቻ ዝውውር መፈፀም እንዳለባቸው ፌዴሬሽኑ አሳስቧል።