ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ እና የጅቡቲ ግንኙነት ልዩ ትርጉም ያለው መሆኑን ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ገለጹ

አዲስ አበባ ሰኔ 30/2015(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ እና የጅቡቲ ሁለንተናዊ ግንኙነት ጥብቅ እና ልዩ ትርጉም ያለው መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ገለጹ።

ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የጅቡቲ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ ቡድንን በጽህፈት ቤታቸው ያነጋገሩ ሲሆን የእራት ግብዣም አድርገውላቸዋል።


 

ዘመናዊ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ባልነበረበት ጊዜም የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስሩ ጠንካራ እንደነበር ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ አስታውሰዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በበኩላቸው የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድኑ የኢትዮጵያ ጉብኝት ስትራቴጂካዊ ግንኙነቱን የበለጠ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል።


 

የጅቡቲ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ መሪና የአገር ውስጥ ሚኒስትር ዴኤታ ሲራጅ ኦማር በበኩላቸው የሕዝብ ለሕዝብ ትስስሩ በንግድ መስክም እንዲጠናከር ሁኔታዎችን ማመቻቸት ያስፈልጋል ብለዋል።


 

የጅቡቲ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ በኢትዮጵያ ቆይታው በአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር እና በውይይት መድረኮች ሲሳተፍ መቆየቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ይጠቁማል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም