መቻል የውድድር ዓመቱ የመጨረሻ ጨዋታውን በድል አጠናቀቀ - ኢዜአ አማርኛ
መቻል የውድድር ዓመቱ የመጨረሻ ጨዋታውን በድል አጠናቀቀ
አዲስ አበባ ሰኔ 29/2015(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገ የ30ኛ ሳምንት ጨዋታ መቻል ለገጣፎ ለገዳዲን 4 ለ 1 ረቷል።
ሱራፌል አወል በ17ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ለገጣፎ ለገዳዲን መሪ አድርጎ ነበር።
ይሁንና ምንይሉ ወንድሙ በ3 እና በ67ኛው ደቂቃ እንዲሁም ግሩም ሐጎስ በ58ኛው እና ዮሐንስ መንግስቱ በ73ኛው ደቂቃ ያስቆጠሯቸው ግቦች መቻልን አሸናፊ አድርገዋል።
ውጤቱን ተከትሎ መቻል በ40 ነጥብ ከነበረበት 11ኛ ደረጃ ወደ 8ኛ ከፍ ብሏል።
አስቀድሞ ከሊጉ መውረዱን ያረጋገጠው ለገጣፎ ለገዳዲ በ18 ነጥብ 15ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።
ቀን ላይ በአዳማ ከተማ በተካሄዱ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ወልቂጤ ከተማ ከአዳማ ከተማ እንዲሁም ሃዋሳ ከተማ ከአርባ ምንጭ ከተማ በተመሳሳይ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ውጤቶቹን ተከትሎ አርባ ምንጭ ከተማ ከሊጉ የወረደ ሲሆን ወልቂጤ ከተማ ደግሞ በሊጉ መቆየቱን አረጋግጧል።