ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በየደረጃው ያጋጠሟትን ፈተናዎች ተሻግራ ብሔራዊ ጥቅሟን ማስጠበቅ ችላለች-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

 

አዲስ አበባ ሰኔ 29/2015 (ኢዜአ)፦ "ኢትዮጵያ በየደረጃው ያጋጠሟትን ፈተናዎች ተሻግራ ብሔራዊ ጥቅሟን በብቃት አስጠብቃለች " ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

አቶ ደመቀ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየሶስት ወሩ ከሚታተመው " ዲፕሎማሲያችን "መጽሔት ጋር  ቆይታ አድርገዋል።

በቃለ ምልልሳቸው በተለያዩ ጉዳዮች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እየተከናወኑ ያሉ የለውጥ እና ተቋማዊ ማሻሻያዎች እንዲሁም ባለፉት ሁለት ዓመታት ከዲፕሎማሲ አኳያ ኢትዮጵያ ገጥሟት ስለነበረው ጫና እና መንግስት ስለወሰዳቸው  እርምጃዎች ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት ፤ አገራዊ ጥቅም እና ሉዓላዊ አንድነት እንዲጠበቅ መንግስት ከአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን የተሻገራቸው በርካታ የዲፕሎማሲ ድሎችን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።

በተለይም ዓለም አቀፋዊ ጫናን በመቋቋም አሁን ለተገኘው ሰላም እና አገራዊ አንድነት በየደረጃው ያጋጠሙትን ፈተናዎች በመሻገር የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ መቻሉን መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም