የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ የጅቡቲና የታጁራ ወደቦችን ለመጠቀም የሚያስችል ኮሪደር በመሆኑ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ያደርገዋል-- ርዕሰ መስተዳድር ሀጂ አወል አርባ - ኢዜአ አማርኛ
የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ የጅቡቲና የታጁራ ወደቦችን ለመጠቀም የሚያስችል ኮሪደር በመሆኑ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ያደርገዋል-- ርዕሰ መስተዳድር ሀጂ አወል አርባ
አዲስ አበባ ሰኔ 29/2015(ኢዜአ)፦ የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ የጅቡቲና የታጁራ ወደቦችን ለመጠቀም የሚያስችል ኮሪደር በመሆኑ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ያደርገዋል ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሀጂ አወል አርባ ገለጹ።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን 5ተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብርን የክልሉ ፕሬዚዳንት፤ ከፍተኛ አመራሮች፤ ባለሀብቶችና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ አስጀምሯል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር ሀጂ አወል አርባ የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክን ለኢንቨስትመንት ይበልጥ ተመራጭ የሚያደርገው የጅቡቲና የታጁራ ወደቦችን ለመጠቀም የሚያስችል ኮሪደር በመሆኑ ነው ብለዋል።
ርዕሰ-መስተዳድሩ አክለውም አፋር ክልል ላይ ጥቁሩም ነጩም እንዲሁም የየትኛውም ሀገር ሰው ኢንቨስት ቢያደርግ የክልላችን አንድ አካል አድርገን ተንከባክበን እንቀበላለን ብለዋል።
ሰመራ የጅቡቲና የታጁራ ወደብን ለመጠቀም የሚያስችል ኮሪደር መሆኑ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ቦታ እንደሚያደርገውም ነው ርዕሰ-መስተዳድሩ የገለፁት።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብርን በአፋር ክልል ሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በማድረጉ ክብር ይሰማናል ብለዋል።
በአጋጣሚው ሶስት ተጨማሪ ባለሀብቶች ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ ኮርፖሬሽኑ ላደረገው አስተዋፅኦም ርዕሰ-መስተዳድሩ ማመስገናቸውን የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መረጃ ያመላክታል።