ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ሰኔ 29/2015 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 28ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ካነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ሰኔ 29/2015 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 28ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ካነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ሰኔ 29/2015 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 28ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ካነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች
👉በዘንድሮው በጀት ዓመት ቢያንስ 7.5 በመቶ ዕድገት እንደሚመዘገብ ይጠበቃል፤
👉ኢትዮጵያ ከፍተኛ የስንዴ አምራች ሀገር መሆኗን አፍሪካ አምኖ ተቀብሏል፤
👉የዋጋ ንረት እንደ ኮሮና ወረርሽኝ ነው፡፡ በዋጋ ንረት የማይሰቃይ ሀገር የለም፤
👉የምንከተለው የሞኒተሪ ፖሊሲን የማጥበቅና የገንዘብ አቅርቦትን የመቀነስ ስራ ቀጣይ የራሱ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፤
👉የኢትዮጵያ ዕዳ በአሁኑ ወቅት ከጠቅላላው የሀገር ውስጥ ምርት 38 በመቶ ደርሷል፡፡ በሚቀጥሉት ሶስት አመታት ከ30 በመቶ በታች ለማድረስ እየሰራን እንገኛለን፤
👉ኢትዮጵያ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አሁንም በኢኮኖሚ አንደኛ ናት፤
👉በዚህ በጀት ዓመት ገቢያችን በ26.1 በመቶ፣ ወጪያችን ደግሞ በ13.4 በመቶ አድጓል፤
👉ገቢን በተመለከተ የእኛ የመሰብሰብ አቅም ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገሮች ግማሽ ነው፤ ገቢን ማሳደግ ገና ብዙ ሰፋፊ ስራዎችን መስራት ይጠበቅብናል፤
👉ከነበረብን ሰፊ የገቢና የወጭ ሚዛን መዛነፍ ውስጥ የገቢ ንግድ ከ13 በመቶ ወደ 9.8 ዝቅ ብሏል፤
👉የባንክ ቁጠባ ደብተር ያላቸው ሰዎች 100 ሚሊዮን ደርሰዋል፡፡ የባንኮች ካፒታልም ከ1.2 ትሪሊዮን ወደ 2.9 ትሪሊዮን አድጓል፤
👉ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር፣ ገበታ ለትውልድ የተባሉት ፕሮጀክቶች የሚሰሩት ሀገራትን በመለመን ነው፡፡ ገንዘቡ ተበላ እንዳይባል ከፍሬው ይታወቃል፣ ስራው ይናገራል፤
👉ጎርጎራ፣ ኮይሻ፣ ወንጭ እና ሃላላ ኬላም እየተሰሩ ያሉት በተመሳሳይ በልመና ነው፡፡ ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ ለየክልሎቹ እናስረክባለን፤
👉የገቢና ወጪ ክፍተቱን (deficit) ለማጥበብ በታክስ አስተዳደር ሰፊ ስራዎችን መስራት አለብን፤
👉የኢትዮጵያ የኢ-መደበኛ ኢኮኖሚ (informal economy) ሰፊ ስለሆነ፣ ገቢ ላይ ሰፊ ስራ መስራት ይጠበቅብናል፤
👉የሀገራችን የታክስ ገቢ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ ከ10 በመቶ በታች ነው። የሌሎች የአፍሪካ ሀገራት 16 በመቶ ነው፤
👉ፕሮፐርቲ ታክስ ኢትዮጵያ ውስጥ አልተጀመረም፤ አዲስ አበባም አልጀመረም፤
👉አዲስ አበባ የጀመረው የጣሪያ እና ግርግዳ የሚባል ከዚህ ቀደም የነበረው እና በየጊዜው እየተሻሻለ የመጣን ህግ ዘንድሮ ማሻሻያ አድርጓል፤
👉ይሄ የታክስ ምንጭ በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት አምጥቶ ያልተገባ ሀብት ወስዶ ከሆነ ቅሬታ የሚሰማበት ስርአት ስላለ በዚያው ስርአት ቅሬታ ቀርቦ ሊታይ ይችላል፤
👉ከትምህርት ጋር በተያያዘ ጥቂት መዋዕለ ህጻናት በኢትዮጵያ የነበሩ ሲሆን ባለፉት አመታት ከ15,000 በላይ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል፤
👉ከመደመር መጽሃፍ ሽያጭ ከ30 በላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መገንባት ተችሏል፤
👉በአዲስ አበባ በአሁኑ ሰዓት ከ700,000 በላይ የተማሪዎች ምገባ እየተከናወነ ነው፤
👉በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የአይነ ስውራን ትምህርት ቤት እየተገነባ ይገኛል፤ ከ300 በላይ አይነስውራን ተማሪዎች በላይ የመቀበል አቅም አለው፤
👉የመተማመን ዘር የይቅርታን ዘር ያልዘራ ሰው የሰላም አዝመራን አያጭድም፤