የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከተለያዩ ሀገራት ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከተለያዩ ሀገራት ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ሰኔ 29/2015(ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከተለያዩ ሀገራት ሚኒስትሮች ጋር ተወያይተዋል።
አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በአዘርባጃን ባኩ ከተማ እየተካሄደ ባለው የገለልተኛ አገራት ንቅናቄ(ናም) የሚኒስትሮች ጉባኤ ጎን ለጎን ከተለያዩ ሀገራት ሚኒስትሮች ጋር በሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው ከሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ኤልሳዲግ አሊ፣ ከኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱልጣን ቢን ሳድ አል-ሙራይኪ እንዲሁም ከቬትናም ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ ሃንግ ቬት ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም ከሀገራቱ ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት በተለያዩ መስኮች ማጠናከር እንደሚገባ መነሳቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ይጠቁማል።
በአምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በአዘርባጃን ባኩ ከተማ እየተካሄደ ባለው የገለልተኛ አገራት ንቅናቄ(ናም) የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።