የኢትዮጵያ የብድር እዳ ከኢትዮጵያ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት የሚይዘው ምጣኔ ወደ 38 በመቶ ዝቅ ብሏል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ የብድር እዳ ከኢትዮጵያ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት የሚይዘው ምጣኔ ወደ 38 በመቶ ዝቅ ብሏል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
አዲስ አበባ ሰኔ 29/ 2015 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብድር እዳ ከኢትዮጵያ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) የሚይዘው ምጣኔ ወደ 38 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 28ኛ መደበኛ ስብስባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመንግስት የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
ከጥቂት ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ የብድር እዳ ከኢትዮጵያ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) የሚይዘው ምጣኔ 59 በመቶ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገልጸዋል።
ይሁንና በማክሮ ኢኮኖሚው መስክ በተከናወኑ ስራዎች የእዳ ምጣኔ ከጂዲፒው አንጻር ወደ 38 በመቶ ዝቅ ማለቱን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ሆና ያለባትን ብድር በመክፈል ላይ ትገኛለች ብለዋል።
በቀጣይ ሶስት ዓመት ውስጥ የእዳ ምጣኔውን ከ30 በመቶ በታች ዝቅ ለማድረግ መታቀዱን ጠቁመዋል።