የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን የ 7 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን የ 7 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ ሰኔ 28/ 2015 (ኢዜአ) የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን የ 7 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ።
የድጋፍ ስምምነቱ የተደረገው የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው በተገኙበት የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እና በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ ተፈራርመዋል።
ህብረቱ ድጋፉን ያደረገው ኮሚሽኑ እያከናወነ ያለው አገራዊ ምክክር በውጤት እንዲጠናቀቅ በማለም ነው።
በስምምነቱ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራትና የአለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮች በተገኙበት ነው።