የኢትዮ-ጅቡቲ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮ-ጅቡቲ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ ሰኔ 28/2015 (ኢዜአ):- የኢትዮ-ጅቡቲ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የምክክር መድረክ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የስራ ኃላፊዎች፣ የጂቡቲ የአገር ውስጥ ሚኒስትር ዴኤታ ሲራጅ ዑመር የተመራው የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን፣ አምባሳደሮች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
መድረኩ የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ማጠናከር ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያና እና ጅቡቲ ሕዝቦችን ግንኙነት፣ ቀጣናዊ ፍልሰት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ተሞክሮን የሚዳስሱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጹሁፎች ቀርበው ምክክር እንደሚደረገባቸው ተገልጿል።
የጅቡቲ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ትናንት ኢትዮጵያ መግባቱ ይታወቃል።