የፌዴሬሽን ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሪፖርት ማዳመጥ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሪፖርት ማዳመጥ ጀመረ
አዲስ አበባ ሰኔ 28/2015 (ኢዜአ):- የፌዴሬሽን ምክር ቤት እያካሄደ ባለው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ቀድሞ በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖች እና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ያካሄዱትን ሕዝበ ውሳኔ አስመልክቶ ያቀረበውን ሪፖርት እያዳመጠ ይገኛል::
ሪፖርቱን እያቀረቡ የሚገኙት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ ናቸው።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነሐሴ 12/2014 ባካሄደው ሁለተኛው አስቸኳይ ስብሰባ በደቡብ ክልል ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የስድስት ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሕዝብ ውሳኔ አስፈጽሞ ሪፖርት እንዲያደርግ መታዘዙን አስታውሰዋል።
በዚሁ መሰረት የምርጫ ቦርድ ሕዝብ ውሳኔውን በማስፈጸም ያዘጋጀው ሪፖርት እንደሆነም ገልጸዋል::
ምክር ቤቱ በቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።